በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአምቦ ከተማ የምትገኘው የጥንታዊቷ የአምቦ መሰረተ ህይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ለራሳቸው እና ለእቴጌ መነን ማስቀደሻ ከቤተመንግስት ጎን ቢያሰሩዋትም ከጥበቷ የተነሳ ብዙ መዕመናንን ማገልገል ስላልቻለች በአዲስ መልክ ግንባታዋ ላለፉት ሰባት ዓመታት እየተከናወነ ይገኛል፡፡